መንግስት ጦር አዝምቶብናል እናም አዲሱ ኢትዮጵያን እና አዲስ አበባን የማዳን ሃልፊነት ባልደራስ!!

 ethiopian human right commussion
18 July 2022

by Dawit Atreso

የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ ከሁለት ወራት የሃገረ አሜሪካ ቆይታ በኃላ ወደ ሃገር ቤት ገብተዋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲን የማደራጀት እና የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ ወካይ ፓርቲ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል በተለይም በጉዞዋቸው ከፍተኛ የፓርቲው አባላትን እና ደጋፊዎችን በማነጋገር እና ለኢትዮጵያ የሚበጀውን አዲስ አበባን ማዳን እና ባልደራስ ለእውነተኛን ዴሞክራስያዊ ፓርቲን ሃገራዊ ፓርቲ ለማድረግ በታቀደው መሰረት በማወያየት እና ደጋፍ በማሰባሰብ ላይ ነበሩ።

የባልደራስ ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም እንደገለፁት መንግስት በተቀናጀ ሁኔታ ዘመቻ እና አፈና በፓርቲው ላይ ከፍቶበታል። በተለይም በግልፅ በፓርላማ የዛቻ እና የማስፈራራት ቀጥተኛ ጥቃት በአፋኙ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እንደደረሰበት አይዘነጋም።

መንግስት አስቦ እና አቅዶ ባልደራስን ለማጥፋት የተቀናጀ ጥቃት ተጋርጦበታል ። በተለይም ሃላፊዋ ጨምረው እንደገለፁት እራሳቸውን ጨምሮ በእስር ለአንድ አመት ከ ሰባት ወር ያለጥፋታቸው እንደቆዩ እና ይህ አሁን እየታየ የሚገኘው የማፈን እና የአለአግባብ እስር ለውጥ ተብሎ የመጣው መንግስት የየእለት ተግባሩ መሆኑን ገልፀዋል። ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ መንግስት ሁሉንም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በመዳፉ ማስገባቱ እና ባልደራስን ማስገባት ባለመቻሉ ጥርስ እንዲነክስበት አድርጎታል።

ሃላፊዋ ሲቀጥሉም ሃገራዊ ፓርቲ ለመሆን ፊርማ የማሰባሰቡን ሂደት ከጨረስን በኋላ ለምርጫ ቦርድ በማመልከት ሃገራዊ ፓርቲ መሆናችንን አፅድቆታል። በተለይም ፊርማውን ለማስፈረም በምንቀሳቀስበት ወቅት ከአዲስ አበባ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች አፈና እና እስር በአባሎቻችን እና በደጋፊዎቻችን ላይ ወከባ እየደረሰብን ነው። ‘’ እየታሰርንም ቢሆን ከአላማችን የሚያግደን ሃይል የለም ‘’ ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይም የታሰሩ አባሎች እና ደጋፊዎችን በሚመለከት ይህ እስር የጀመረው ከአደዋ እና ካራማራ በዓል አከባበር ቀን በኋላ ነው እስሩ ተጠናክሮ የቀጠለው።